ስለ እኛ (About Us)
ተቋማዊ እሴቶች እና ራዕይ (Institutional Values and Vision)
ተልዕኮ (Mission)
የተቀናጀ የጸጥታ አስተዳደር እና የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ስርዓትን በመገንባት፣ ወንጀልን መከላከል፣ እና ህግና ስርዓት የተከበረባት ከተማ ማድረግ ነው።
ራዕይ (Vision)
በ 2022 አዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት እና ለኑሮ ተመራጭ የሆነች ከተማ ሆና ማየት።
እሴቶች (Core Values)
የህግ የበላይነትን ማክበርና ማስከበር፣ ለላቀ ሰላምና ጸጥታ መትጋት፣ ታማኝነትና ተጠያቂነት፣ ተቋማዊ አጋርነት፣ ፍትሐዊነትና ሰብዓዊነት፣ ሚስጥር ጠባቂነት።
ኃላፊነቶች (Responsibilities)
የቢሮው ስልጣንና ተግባር
- የደንብ ማስከበር ባለሥልጣንን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
- ከተማ አቀፍ ፖሊሲ ይቀርፃል፤ ስትራቴጂ ይነድፋል፤ ህግ ያመነጫል፤
- በፀጥታ ጉዳዮች የከተማው አስተዳደር ዋና የፀጥታ አማካሪ ሆኖ ይሰራል፤
- የግጭት መንስዔዎችን በጥናት ይለያል፣ ግጭት እንዳይከሰት ይከላከላል፤
- ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችን ይቆጣጠራል፤
አገልግሎቶች (Services)
የምንሰጣቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች
የምዝገባና የድጋፍ አገልግሎት
ለብዙሃን ማህበራት እና አደረጃጀቶች የምዝገባና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት።
የሰላማዊነት ማረጋገጫ
አዲስ የኃይማኖት ተቋማት ለሚመሰረቱ አካላት የሰላማዊነት ማረጋገጫ መስጠት።
የድምጽ ብክለት መቆጣጠር
በመኖሪያ አካባቢ የሚፈጠሩ የድምጽ ብክለት ችግሮች ላይ ፈጣን ምላሽ መስጠት።
ጥበቃ ኤጀንሲዎች አስተዳደር
ከግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች የአሰራር ስርዓት ጋር ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት።
መረጃ አሰጣጥ
ፀጥታን የተመለከቱ መረጃዎች ለሚጠይቁ ሕጋዊ ተቋማት ፈጣን ምላሽ መስጠት።
የጦር መሳሪያ ፍቃድ
ለጦር መሳሪያ አጠቃቀምና አያያዝ ፍቃድ አስተዳደራዊ ድጋፍ መስጠት።
Contact Us
ከእኛ ጋር ይገናኙ
የእውቂያ መረጃዎች
ዋና መ/ቤት
አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንጻ ቁጥር ሁለተኛ ፎቅ 41
ስልክ
0115-11-22-33
ኢሜል
peaceaddis123@gmail.com